fbpx

Tsedey Bank S.C

አዲስ ዘመን (May 14, 2022)

የጨረታ ማስታወቂያ 

የቀድሞው አማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም የአሁኑ ፀደይ ባንከ አማ በአማራ ክልላዊ መንግስት ውስጥ በአነስተኛ የፋይናንስ አገልግሎት ሲሰራ ቆይቶ አሁን ከብሄራዊ ባንክ ባገኘው ፈቃድ መሰረት ወደ ባንክ በመሸጋገሩ ለከፈታቸው ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚሰጡ ካውንተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ነጋዴ መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የጨረታው መመሪያ

  • በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቶች በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ በዘመኑ የታደሰ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር መክፈያ ሰርተፍኬት እንዲሁም የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢ የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
  • ተጫራቾች ለሚሳተፉባቸው እቃ አይነት ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በተሰጠው ዶክመንት መሰረት ብቻ ዋጋ መሙላት ይገባቸዋል:: በነጠላ ዋጋና በድምሩ ልዩነት ካለ ነጠላ ዋጋው የሚያዝ ይሆናል፡፡ ዋጋ ሲሞላ ስርዝ ካለ ፊርማ ሊኖረው ይገባል፡፡ ሆኖም ግን ስርዝ ድልዝ የበዛበትና ግልፀኝነት ከጎደለው ተወዳዳሪው ከጨረታው ይሠረዛል።
  • ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል የአጠቃላይ ዋጋውን 2% በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም ሲፒኦ በፀደይ ባንከ አማ ትክክለኛ ስም በማሰራት ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  • ዋጋ በሚሞሉበት ጊዜ ተጨማሪ እሴት ታክስንና እንዲሁም እስፈላጊ የሆኑ ወጪዎችን የማጓጓዣ፣ ማውረጃና መጫኛ/ በማካተት ወይም በመደመር ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ዋጋው ተካቶ እንደተሞላ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
  • ማንኛውም ተጫራች አስፈላጊውን መረጃ አሟልቶ ጨረታውን በወቅቱ አጠናቆ ያላቀረበ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  • አሸናፊው በኦዲት ተረጋግጦ ማሸነፉ በደብዳቤ በተገለፀለት በአምስት /5/ ተከታታይ ቀን ውስጥ የስራ ዋስትና 10% የጠቅላላ ዋጋውን በCPO ወይንም በጊዜ ገደብ ያልተገደበ ዋስትና unconditional bank guarantee በማቅረብ ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡ የሚያመጣው ዋስትና ጊዜ ከስድስት ወር ማነስ የለበትም፡፡
  • አሸናፊ ድርጅቶች አሸናፊነታቸው ተገልፆላቸው ውል ከያዙ በኋላ እቃዎችን በተመለከተ ሙሉ በሙሉ በተከታታይ ቀናት በተጠቀሰው ቦታ በ60 ቀን ውስጥ ሰርቶና ገጥሞ ያስረክባል፡፡ ማስረከቢያ ቦታ በጨረታ ሰነዱ በተገለጹት ቦታዎች ይሆናል፡፡
  • የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር / በመክፈል ከተቋሙ ሂሳብ ክፍል ቢሮ ቁጥር 403 ወይም አዲስ አበባ ፒያሳ ቀይ ባህር የጋራ መኖሪያ ቤት ከሚገኘው ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
  • የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን በአብቁተ ዋና መ/ቤት ባ/ዳር ቢሮ ቁጥር 205 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን በኤንቨሎፕ ውስጥ በማሸግ የተወዳደረበትን እቃ በግልጽ በመጻፍ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል። ጨረታው በዚህ እለት 4፡00 ላይ ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልፅ ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በራሳቸው ፈቃድ ካልተገኙባንኩ ጨረታውን ከመክፈት አይታገድም።

ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ፡- አማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ዋና መ/ቤት ባህር ዳር

ስልክ ቁጥር 058-226-60-08/058-226-25-76

ፀደይ ባንክ አ.ማ